የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ደ/ም/መ/ባ/04/2019
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
| የማሽኑ ዓይነት | የማሽኑ ፈረስ ጉልበት | የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ | የሚጠቀመዉ የነዳጅ ዓይነት | ለአንድ ማሽን የሚፈለገዉ ሰዓት | ብዛት በድስትሪክት | ||
| ቦንጋ | ታርጫ | ሚዛን | |||||
| ዶዘር | 305 እና በላይ | 2012 እና በላይ | ናፍጣ | 1200 | 2 | 2 | 2 |
| ኤክስካቫተር | 247 እና በላይ | 2016 እና በላይ | ናፍጣ | 1200 | 1 | 1 | 1 |
| ሮለር | 140 እና በላይ | 2013 እና በላይ | ናፍጣ | 800 | 2 | 2 | 2 |
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል:-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ እንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዩ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበርያዉንም ለያንዳንዱ ሎት በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ ::
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነዉ በጨረታ ሰነድ ዉስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታዉ ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛዉም አቅራቢ ክፍት ነው::
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው ከቀኑ 11:30 ድረስ ይሆናል:: ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3:00 ተዘግቶ በዕለቱ ጧት 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል :: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም ::
- ተጫራቾች በጨረታዉ ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸዉን ማቅረብ አለባቸዉ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ዉጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም ::
- ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 /0474527727 ደዉለዉ ማነጋገር ይቻላል::
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
✨ messages.ai_summary
South West Ethiopia Peoples' Region Roads Authority seeks suppliers to rent bulldozers, excavators and rollers for road construction and maintenance projects, with machines meeting specified horsepower, year and fuel requirements. Open to all suppliers regardless of nationality; bidders must submit tax clearance, business licence, supplier certificate, VAT registration, TIN and tax office support letter, plus prior good performance.
