የሆቴልና የስልጠና አዳራሽ አገልግሎት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ - OMNI Ethiopia (AMIRP Forward Media Fellowship Program)
OMNI Ethiopia (ኦምኒ ኢትዮጵያ)
የሆቴልና የስልጠና አዳራሽ አገልግሎት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
OMNI Ethiopia በ AMIRP Forward Media Fellowship Program ስር በሚቀጥሉት ሁለት አመታት በ40 ዙር ለሚያካሂዳቸው ተከታታይ የስልጠና፣ የወርክሾፕ እና ተያያዥ ዝግጅቶች በድምሩ ከ1,000 በላይ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችል የሆቴል፣ የስልጠና አዳራሽ እና ተያያዥ የመስተንግዶ አገልግሎት ከብቁ አገልግሎት ሰጪዎች ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማምረጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣ ለጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
- የተጫራቾች ብቃት
ተጫራቾች፡-- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የTIN ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
- የVAT፣ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና
- ተመሳሳይ የሆቴል፣ የስልጠና ወይም የኮንፈረንስ አገልግሎት የመስጠት ተገቢ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የስልጠና ቦታ መስፈርቶች :-
ለስልጠናዎቹ የሚቀርበው ቦታ ቢያንስ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፡-- ተሳታፊዎችን በምቾት ማስተናገድ የሚችል በቂ ስፋት ያለው የስልጠና አዳራሽ፤
- ለቡድን ውይይቶች፣ ለምምዶች እና ተግባራዊ ስልጠናዎች ተስማሚ የሆኑ አነስተኛ/ Breakout አዳራሾች፤
- በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው መሆን ይመረጣል።
- የኢንተርኔትና የቴክኖሎጂ አገልግሎት
- ፈጣን፣ የተረጋጋ እና ብዙ ተጠቃሚዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል Wi-Fi/ internet፤
- Zoom፣ Microsoft Teams ወይም ተመሳሳይ የቨርቹዋል ስብሰባ መድረኮችን ለመጠቀም ተስማሚ የኢንተርኔት ጥራት፤
- Projector/Screen፣ የድምፅ ማጉያ እና አስፈላጊ የAudio-Visual መሳሪያዎች።
- የምግብ፣ መጠጥና መስተንግዶ አገልግሎት
የአገልግሎቱ ዋጋ የሚከተሉትን ጨምሮ መቅረብ አለበት፡-- የጠዋት እና የከሰዓት በኋላ ቡና/ሻይ፣ ወተት እና ተያያዥ መስተንግዶ፤
- ምሳ፤
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ፤
- እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ተያያዥ የመስተንግዶ አገልግሎቶች።
- የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ከአስፈላጊ ህጋዊ ሰነዶች ጋር ከ18/01/2019 ዓ.ም እስከ 22/01/2019 ዓ.ም ድረስ በድርጅቱ ኢ-ሜይል omni-ethio@gmail.com መላክ ይኖርባቸዋል። - የአሸናፊ ተጫራች ማሳወቂያ
OMNI Ethiopia የጨረታውን ውጤት እና ያሸነፈውን ተጫራች በኢ-ሜይል ያሳውቃል። - የዋጋ ማቅረቢያ
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እያንዳንዱ አገልግሎት፡-- የአንድ ተሳታፊ ዋጋ (Unit Cost) ፣
- በተጠበቀው የተሳታፊ ብዛት መሠረት አጠቃላይ ዋጋ (Total Cost) በግልጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የዋጋ አቀራረብ
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ VAT እና Service Chargeን ጨምሮ የመጨረሻ ዋጋ መሆን አለበት። - የጨረታ መሰረዝ መብት
OMNI Ethiopia የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ፡- 0919 19 6420 / 0988 136 968 / 0923 161 696
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከላይ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች ሊያገኙን ይችላሉ።
ኦምኒ ኢትዮጵያ/OMNI Ethiopia
✨ messages.ai_summary
OMNI Ethiopia seeks qualified providers for hotel, training hall, and hospitality services for over 1,000 participants across 40 training and workshop rounds. Bidders need a renewed business license, TIN, VAT registration, and relevant experience. Venues must have breakout rooms, reliable Wi-Fi, AV equipment, and catering.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
