Tender Detail

Tender Details

  • Company የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሲሆን ከአዲስ አበባ እስከ ሻምቡ አስፋልት 322 ኪሎ ሜትር ከሻምቡ እስከ አሙሩ 72 ኪሎ ሜትር ፒስታ በአጠቃላይ 394 ኪሎ ሜትር : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0917078125
  • Website
  • Deadline10 Oct 2026, 5:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ)
  • Bid Security20,000 ብር (ሃያ ሺህ) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO)
  • opening dateበ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብስ፣ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣ የንፅህና ዕቃዎች፣ ፈርኒቸርና ጎማ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።

የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብስ፣ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣ የንፅህና ዕቃዎች፣ ፈርኒቸርና ጎማ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡-

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2019 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሰ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በግልጽ የሚታዩ ህጋዊ ማስረጃዎችንና ከሚመለከታቸው የምስክር ወረቀቶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው መካፈል ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም የተገለጹትን ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል በሕግ የተከለከለ ነው።
  5. የጨረታው ሳጥን የሚቆየው 15 የሥራ ቀን ከ15/01/2019 እስከ 05/02/2019 ዓ.ም ክፍት ሆኖ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. መስሪያ ቤቱ ከአጠቃላይ ግዥ 3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ (with holding tax) እና 7.5% ቫሊው አድድ ታክስ (value added tax) የሚቆርጥ መሆኑን አቅራቢው ድርጅት ማወቅ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሰነዱ አይነት 20,000 ብር (ሃያ ሺህ) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር ቴክኒክ ፖስታ ውስጥ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከህሎት የሚቀርብ ደብዳቤ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይገባሉ። እንዲሁም አሸናፊው ውል በሚገቡባቸው ዕቃዎች አጠቃላይ ዋጋ ውል ማስከበሪያ 2% ያስይዛሉ የተዋዋሉበትን ንብረትም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  9. በሳንፕል የሚቀርቡ ዕቃዎች ትልቅ አጀንዳ መካከለኛ አጀንዳ የደንብ ልብስ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ኦሪጅናል ሪስት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ በየሰነዱ አይነት በማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ) ከአሙሩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. የጨረታው ሰነድ financial document እና technical document በየፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡ እንዲሁም ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ መጻፍ አለበት።
  14. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  15. መስሪያ ቤቱ የገዛቸውን ዕቃዎች የሚረከበው በአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ወረዳችን የምትገኘው በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ሲሆን ከአዲስ አበባ እስከ ሻምቡ አስፋልት 322 ኪሎ ሜትር ሻምቡ እስከ አሙሩ 72 ኪሎ ሜትር ፒስታ በአጠቃላይ 394 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ0917285202 ወይም 0900540448 ላይ ደውለው መረዳት ይቻላል።

የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Amuru District Finance Office seeks legal bidders to supply uniforms, stationery, sanitary items, furniture and rubber goods for district offices. Bidders need a valid trade licence, tax clearance, VAT registration, supplier registration and must submit samples of uniforms.
Save Tender