የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሲያሟሉ የሚችሉ ፈላጊዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ በባንክ የተረጋገጠ [የተመሰከረ] ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ወንድ፤ ጋር ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፤ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው፤ ብር 500 (አምስት መቶ ብር)፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በከተማ አስተዳደሩ አካውንት ገቢ በማድረግ፤ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ፤ አንድ አሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ፣ በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 [ማዥኬዝ ቲም] ሰዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሽጎ፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ በሌሉበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን፤ የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የቃላት እና የቁጥር ልዩነቶች የሚያጋጥም ከሆነ፤ በጨረታ ሰነዱ ላይ ላለው በላይነት ይኖረዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ፤ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Hawassa City Administration Finance Department seeks to sell various disposable assets via open bid. Bidders must meet listed requirements and submit a bank-certified CPO or bid bond. The department reserves the right to cancel the tender fully or partially.
