Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
  • Address , Phone: 0115549304
  • Website
  • Deadline18 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 1000.00 (አንድ ሺህ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡30
  • Categories Spare Parts , Machinery , Other Sales

ለሁስተኛ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ ማሽነሪዎችና መስዋወጫዎች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DIS 01/2019


ለሁስተኛ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ ማሽነሪዎችና መስዋወጫዎች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DIS 01/2019

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻ ማሽኖችን፤ የተርሚናል ትራክተሮችን፤ ሪችስታከሮችን፤ የማሽን ሞተር ፓርትን፤ የማሽን ጊርቦክስ ፓርትን እና የማሽነሪ አታችመንት የሆኑ ፔፐር ሮል ክላምፕ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ተዘግቶ እስከ ሚታሸግበት ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሠዓት ከ 8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት 3ኛ ፎቅ በመከፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ንብረቶቹን ለማየት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሠዓት ከ 8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት በአካል በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በክፍል ሁለት ላይ በሚፈልጉት የንብረት አይነት ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ተ.እ.ታ ጨምሮ በመሙላት እና ለሚወዳደሩበት የንብረት አይነት የተቀመጠውን 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ በተቋሙ ትክክለኛ ስም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (Ethiopian Shipping & Logistics) በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

በጨረታ መከፈቻው ሰዓት፣ አለትና ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ነገር ሲገጥመው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549304/0906329086/0951414225 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Shipping & Logistics invites bids for the second-round public auction sale of used empty container handlers, terminal tractors, reach stackers, machine engine and gearbox parts, and paper roll clamps. Bidders may inspect items at Kality Port and Terminal and Mojo Logistics Center.
Save Tender