Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዋሽ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline23 Sep 2026, 9:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ) ብር
  • opening dateለግልጽ ጨረታ በ13/01/2019 እና 16/1/2019 ጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00
  • Categories Other , Disposal Sale , Other Sales

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ13/01/2019 ዓ/ም እና 16/01/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ13/01/2019 ዓ/ም እና 16/01/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ እካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 13/01/2019 ዓ/ም እና 16/01/2019 ባሉት ቀናት ለግልጽ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ እካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ የጨረታ ቦታ የጨረታ ዓይነት ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ቃሊቲ ጉምሩክ ግልጽ እና ሃራጅ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ለግልጽ ጨረታ ለግልጽ ጨረታ እስከ በ13/01/19 ረቡዕ እና 16/01/2019 ቅዳሜ ጠዋት 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4:45 ለግልጽ ጨረታ በ13/01/2019 እና 16/1/2019 ጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00
  1. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ የጨረታ ቦታ የጨረታ ዓይነት ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ቃሊቲ ጉምሩክ ግልጽ እና ሃራጅ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ለግልጽ ጨረታ ለግልጽ ጨረታ እስከ በ13/01/19 ረቡዕ እና 16/01/2019 ቅዳሜ ጠዋት 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4:45 ለግልጽ ጨረታ በ13/01/2019 እና 16/1/2019 ጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00
  1. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፦ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  4. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Office seeks to sell various confiscated contraband goods—shoes, clothes, cosmetics, car spare parts, electrical items, mobile cases, food, and more—via open and auction bids at Kaliti Customs. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, tax clearance, and recent certificate.
Save Tender