በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ _09 የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ፦
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መስያ ቁጥር 001/ 2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ _09 የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ፦ ሎት 1፡-የደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅና የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 2፡ -አላቂ የትምህርትና የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3፡-የህትመት ስራዎች፤ ሎት 4፡-ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የፅዳት ዕቃዎችን)፤ ሎት5፡- ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮን መለዋወጫ፤ ሎት6፡-የፕላንት ማሽነሪ(ኤሌክትሪክ/ኤሌክትሮኒከስ) ጥገና ሎት7፡-ለህንፃ ቁሳቁስ (የውሀ መለዋወጫ የግንባታ ዕቃዎች)፤ ሎት8፡- ለመስተንግዶ የሚውል አቅርቦት እነዚህን ዕቃዎች እና ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንደሚችሉ ይጋብዛል። ይፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚፈልጉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያለው፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸው በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ WWW.PPagOV.et ላይ መመዝገብ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎቸ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንክ ስም በደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስም CPO በማሰራት ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
| ሎት | ሎት1 | ሎት2 | ሎት3 | ሎት4 | ሎት5 | ሎት6 | ሎት7 | ሎት8 |
| ብር | 2,400 | 2,570 | 800 | 2,510 | 4,500 | 1,100 | 1,160 | 1,500 |
የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለአሸነፉበት ዕቃ የሚፈፅሙት ማንኛውም ወጪ በራሳቸው በመሸፈን በሚሠጣቸው አሸናፊነት መሰረት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ማንኛውም የመንግሥት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነማጓጓዣቸው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው::
8. ከላይ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶቸ የሚያሟላ ተጫራች ካለ የማይመለስ ብር 400.00(አራት መቶ ብር) በመከፈል የተጫራቶች መመሪያ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ (ሶስት) ቀን በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ለማይቀርብባቸው የዕቃ አይነቶች ስፔስፊኬሽን ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሰጠ ልዩ አስተያየትን ተግባራዊ ያደርጋል የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ መመለስ ይኖርበታል:: የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
10. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦሪጂናል ከአንድ ኮፒ ጋር ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ በሚገኝበት አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አውቶቢስ ተራ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው::
11. ጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት በዚሁ ቀን በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 4:00 ላይ መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል:: ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል:: ከዛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::
12. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0112-13-73-57/0112-73-59-74 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
