ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ ሎት ሁለት የህትመት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ ሎት ሁለት የህትመት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
| ተ.ቁ | የዕቃው አይነት | መለኪያ | ምርመራ |
| 1 | ሎት አንድየመኪና መለዋወጫ ዕቃ | በቁጥር | የሎት አንድ እና የሎት ሁለት ዕቃዎች ብዛትእና ዓይነትዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል። |
| 2 | ሎት ሁለት የህትመት አገልግሎት ግዥ | በቁጥር |
ተጫራቶች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ እና ሌሎች ያሏቸውን ማስረጃዎቻቸውን በግልጽ ሲነበብ በሚቻል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቶች የጨረታውን ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከግዥ/ፋ/ገብ/አስ/ ዳይሬከቶሬት አጠገብ ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ፣ ቢሮ ቁጥር 18 ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት CPO ብቻ ለእያንዳንዳቸው ሎት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ፕሮፎርማ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒና አርጅናል በአንድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ጨረታው ከታወጀበት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ገብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 ሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎጊታ አጠገብ ሀዋሳ ይከፈታል ።
- መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን (ብዛት) ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሲቀንስ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታው ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመከፈት ሥነሥርዓት የሚከናወነው በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916025922 ወይም 0912462506 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Sidama National Regional State Culture, Tourism and Sports Bureau seeks to procure Lot 1 vehicle spare parts and Lot 2 printing services via national open tender. Bidders must be engaged in these sectors and submit a renewed business license, supplier registration certificate, VAT certificate, taxpayer registration certificate, and commercial registration certificate.
