Tender Detail

Tender Details


ልዩ ልዩ የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች የውሀ መስመር፤ የመብራት መስመር፤ የፍሣሽ መስመር AT ጄኔሬተር /6244/


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር/ ገ/ጨ 001/ 2019 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችንና የጥገና ግብዓቶችን፡- በአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ፤
  5. በኣቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ በዌብሳይት የሚረጋገጥ፤
  6. እንደአስፈላጊነቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ለህክምና ዕቃዎች ግድ ነው
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ፋዐ7 በሚገኘው የግዢ ክፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤና ጣቢያው ስም በተከፈተው መደበኛ የሂሣብ ቁጥር 1000056592141 ገቢ በማድረግ ባንኩ የሚሰጠውን ደረሰኝ በማያዝ ወይም በጥቃቅንን እና አነስተኛ ለተደራጁ ከአደራጃቸው ወረዳ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ በማምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርበት ዕቃዎች ናሙና በዕቃው ዓይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
  9. ተጫራቾች ከተቋሙ በወሰዱት ሰነድ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዋና እና ኮፒ ሠነዶችን እንዲሁም ለናሙና የሚቀርቡ የዕቃውን ስም የሚገልፁ የዕቃዎች ናሙና እና የፎቶግራፎች ናሙና ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን፡-

 

የሎት ቁጥር የሎት መግለጫ የጨረታ ማስከበሪያ % የጨረታ ማስከበሪያ በብር
ሎት1 የደንብ ልብሶች ግብዓቶች /6211/ 0.5 9,000.0
ሎት2 የደንብ ልብስ የስፌት አገልግሎት /6211/ 0.5 1,000.00
ሎት3 አላቂ የጽህፈት /6211/ 0.5 8,500.00
ሎት4 የህትመት ውጤቶች /6213/ 0.5 5,000.00
ሎት5 ቀሚ እና አላቂ የህክምና /6213/ 0.5 20,000.00
ሎት6 ያለፈባቸው መድሀኒቶች የማስወገድ አገልግሎት/6214/ 0.5 15,000.00
ሎት7 የካፌ አገልግሎት የሚሰጥ 0.5 14,000.00
ሎት8 የጽዳት ዕቃዎች /6218/ 0.5 7,500.00
ሎት9 ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መሳሪያዎች/6219/   5,000.00
ሎት10 ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የጥገና  እና የሰርቪስ አገልግሎቶች/6243/ 0.5 1,500.00
ሎት11 ልዩ  የጥገና ዕቃዎችን/6243 እና 6244/ 0.5 3,000.00
ሎት12

ልዩ ልዩ የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች የውሀ መስመር፤ የመብራት መስመር፤ የፍሣሽ መስመር AT ጄኔሬተር /6244/

0.5 2,000.00
ሎት13 ኤሌክትሮኒከስ የሆኑ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/6313/ 0.5 15,000.00
ሎት14 ፈርኒቸር የሆኑ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/633/ 0.5 5,000.00
ሎት15 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች 0.5 2,000.00

 

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በዘረፉ ከተደራጁበት ወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሠነድ መቀበያ ጊዜ የበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዚያው ዕለት እና ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ 3፡30 የመከፈቻ ቃለጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል። በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያውንም ሆነ መከፈቻ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማራዘም አይቻልም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር:- 02-29-12-50 ወይም በኢሜይል አድራሻችን፡- akw8hc@gmail.com ወይም ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ አድራሻ፡- ከአውቶብስ ተራ ወደ ሰባተኛ ወይም ከሰባተኛ ወደ አውቶብስ ተራ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ሲሄዱ ከዋይ ዜድ ህንፃ ወደ መካነ ሠላም ሆቴል በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ያህል አንደሄዱ ባለ አራት ፎቅ ሀንፃ ላይ /በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በሚል ስያሜ ያገኙናል፡

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Procurement of various maintenance and service works for water lines, electrical lines, sewer lines, and AT generators, plus related goods and services across 15 lots. Open to legally licensed bidders with valid business license, tax compliance, MoF registration, supplier list registration, and professional competency certificates for medical items. Samples required.
Save Tender