በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብሶች፣የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፤የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች፣የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ፈርኒቸሮች፤ላይ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብሶች፣የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፤የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች፣የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ፈርኒቸሮች፤ላይ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው ሆኖ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ዌብሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት ዌብሳይት ላይ መገኘታቸውን የሚያመላከት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 የደንብ ልብሶች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000(አስር ሺህ ብር) ብቻ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂና ቋሚ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ብቻ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ ሎት 4 የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ ሎት 6 ፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በብር ወይም CPO በማስያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት በያንዳንዱ ሎት ከሚመለከተው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት ብር ወይም CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተምም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሰነዱ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16) የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ጉምቢቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ ከ አዲስ አበባ በሰንዳፋ በኩል 65 ኪ.ሜ ሲሆን በደብረ ዘይት 81 ኪ.ሜ
ስልክ፡- 0912230467 ወይም 0911360403 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of uniforms, office supplies, consumable and fixed office items, cleaning materials, vehicle parts and tires, electronics, and furniture for various sector offices in East Shewa Zone. Bidders must hold a valid trade license, pay taxes, be VAT-registered with a TIN, and be registered on the federal or regional supplier database.
