የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ኮምፒተሮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎች ግዢ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሸዋ ዞን የመተሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስሪቅ ሸዋ ዞን የመታሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መስሪያቤቶች ለ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን በአዲሱ የመንግስት የግዢ መዋቅር የስራ ሂደት መሰረት ግዢ ለመፈጸም እና በስራ ላይ ለማዋል እንዲቻል አገልግሎት ሊሰጡከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ማለትም፤
1. የጽዳት እቃዎች
2. የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች
3. የሰራተኛ የደንብ ልብስ
4. የጽህፈት መሳሪያዎች
5. ኮምፒተሮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
6. ሞተር ሳይክሎች ሲሆኑ
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈረቶች የሚያማሱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ከላይ 1-6 የተጠቀሱትን እቃዎች አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) የመታሃራ ከታማ ገንዘብ ጽ/ቤት 1000060727377 ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
2. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ያመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በመታሀራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
3. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 022 226 0649 ይደውሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሸዋ ዞን የመታሃራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
