Tender Detail

Tender Details

  • Company በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ገዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: 0911803882/ 0944788773 /0900262969 & 0972871266
  • Website
  • Deadline28 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 600.00 (ስድስት መቶ) ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ (ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች)፤ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ (ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ለፅዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ)
  • Bid Securityብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ለእያንዳንዱ ሰነድ (ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ለደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች)፤ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ) ለእያንዳንዱ ሰነድ (ለፅዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር)፤ በከፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ ፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎች ግዢ

በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ገዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ ፈርኒቸር አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት ዕቃዎች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ለጽሕፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ)፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለፅዳት እቃዎች፣ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000064687607 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ በወረዳው የስብሰባ አዳራሽ ወይም በግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ይህ ቀን በዓል ወይም ሰንበት ለይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ለደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) እንዲሁም፤ ለፅዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ) ፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ አቅምች ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ኦጎልቾ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ስ.ቁጥር 0911803882, 0944788773 0900262969 & 0972871266

በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ገዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of office electronics, furniture, stationery, cleaning supplies, uniforms, and vehicle tires for district offices via open tender. Bidders must hold valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier certificates. Delivery required to Ogolcho town at bidder's transport cost.
Save Tender