Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከ/ፐ/ሰ/የሠ]ሀ/ል/ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline08 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security40,000.00
  • opening date2026-07-08 10:30:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፐብሊከ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ማወዳደር ይፈልጋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከ/ፐ/ሰ/የሠ]ሀ/ል/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/ቃ/ፐ/006/2018


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፐብሊከ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ማወዳደሪያ መስፈርቶች

1. የህጋዊነት ጉዳዮች በተመለከተ ዕጩ ተወዳደሪዎች በዘርፉ ማለትም በሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት ዘርፉ የግብር ከፋይነት ምዝገባ እንዲሁም የተ.እ.ታ (ቫት) ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ የንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከላይየተሰጡትን መስፈርቶች ማሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም 6 ወር ያላለፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. የስራ ልምድ በሬስቱራንት ፣በባርና ሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት የስራ አገልግሎት ዘርፍ ከ1 ዓመት በላይየስራ ልምድ ያለውና አሁንም በዘርፉ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል

3. የሰው ሀይል ድርጅቱ ቢያንስ 2000 ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችል የሆቴል መስተንግዶ የሰው ሀይል መዋቅር አደረጃጀት ያለውና ማናጀር፣ ሼፎች/ምግብ አዘጋጆች/፣ አስተናጋጆች ወዘተ መዋቅር ያለውና በድምሩ ቢያንስ 13 ሰራተኛ ያለው

4. የተሽከርካሪ ሁኔታ ድርጅቱ አገልግሎቱን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን እንዲችል የሚያስችሉት ተሽከርካሪዎች ያለው ለምሳሌ ግብዓት ሊያቀርቡ የሚችሉ የጭነት ተሽከርካሪ ወዘተ ያለው

5. ተፈላጊ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሲሆን (CPO ሲያሰሩ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ብለው ያሰሩ)

6. በድርጅቱ የሚሸፈኑ ግብዓቶችን በተመለከተ ድርጅቱ የውሃ፣ የመብራት እንዲሁም የቤት ኪራይ የማያስከፍል መሆኑ እና ድርጅቱ የራሱ እቃዎች ያሉት መሆኑ እና አሸናፊው አካል የራሱን ተጨማሪ እቃ በማስመዝገብ አስገብቶ መስራት የሚችል መሆኑ

7. የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም ቢያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO /የባንከ ዋስትና /በጽ/ቤታችን ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል

8. ለመንግስት ንብረት ጥንቃቄ በማድረግ በሚሰራና በራሱ ወይም በሰራተኞቹ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በመገልገያ ቁሳቁስና ህንጻ ላይ ብልሽት ቢደርስ ወይም ጥፋት ቢከሰት መልሶ ለመተካት አልያም ካሳ ለመከፈል ፍቃደኛ መሆኑን ማረጋገጫ ደብዳቤ በድርጅቱ ፈርማ እና ማህተም ማረጋገጥና ማቅረብ የሚችል፡፡

9. ለካፌ ለሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ( 10 ) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተጫራቾች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 508 ጨረታው ይከፈታል፡፡

11.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች ላሸነፉት ግብዓት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 30% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ አድራሻ፡-
ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይቻላል፡፡


የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE