Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011 122 64 56
  • Website
  • Deadline02 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2026-07-02 10:30:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት- 01 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሎት 02 የሠራተኞች የመዝናኛ ከበብ የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07/2018



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት- 01 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሎት 02 የሠራተኞች የመዝናኛ ከበብ የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.
ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያቢቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው

2.
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ ለሎት1 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ ) ለሎት 02, ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

3.
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ዳይሬከቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከቢሮአችን ቢሮ ቁጥር 101 በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ፣ በፍላሽ ወይም በኢሜል መውሰድ ይችላሉ፣

4.
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ለሁለቱም ሎቶች ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣

5.
ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣

6.
የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣

7.
የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

8.
አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት እቃዎቹን በማቅረብ ለቢሮ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፣

9.
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።


ለተጨማሪ መረጃ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
በስልክ ቁጥር 011 122 64 56 አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE