Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline06 Jul 2026, 8:30 AM
  • magazineadiss zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security300,000.00
  • opening date2026-07-06 15:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) ፣ ለሠራተኛ ካፍቴሪያ፣ ለኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እና ላውንጅ አገልግሎት የሚውል የተፈጨ እና የተቆላ ቡና አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T621

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) ፣ ለሠራተኛ ካፍቴሪያ፣ ለኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል እና ላውንጅ አገልግሎት የሚውል የተፈጨ እና የተቆላ ቡና አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የሦስት (3) ዓመት ውል በመግባት አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1. በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታከስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል (የፐIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ ሁለት (2) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይየሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T621 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሦስት መቶ ሺህ ብር(300,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንከ ዋስትና ወይም በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለበት። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ውስንነት ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም 2፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መሥሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ብርቱካን ሰሙ
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552

ኢ-ሜይል: birtukans@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

Save Tender