Tender Detail

Tender Details

  • Company የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ
  • Address በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116720000
  • Website
  • Deadline10 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security10,000.00 /አስር ሺህ/ ብር
  • opening date2026-06-10 14:30:00
  • Categories Food And Beverage , Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes , Sport Materials And Sportswear

በፈዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ፣ የተለያዩ ሰፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ፣ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ ከስክስ ጫማ እና ሸራ ጫማ ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በፈዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ

1ኛ. የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ

2ኛ. የተለያዩ ሰፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ፣ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ ከስክስ ጫማ እና ሸራ ጫማ ግዥ

በማስፈለጉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የአገር ውስጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገንዘብ ሚ/ር የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬትና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ መመሪያና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የሆነውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሠዓት ከአ/አበባ በደብረብርሃን መስመር 63 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፖሊስ ማሠ ተቋም ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

 

ተ.ቁ

የእቃው ዓይነት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

1

የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ ግዥ

ሰኔ 03/10/2018 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል

2

የተለያዩ ሰፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ፣ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ እና ሸራ ጫማ ግዥ

ሰኔ 04/2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል

 

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ በባንክ ተረጋግጦ በሚሰጥ (CPO) በማሠራት የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታ ውስጥ በማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ጨረታ ሠነድ በአማርኛ መሆኑን እየገለፅን፤ መ/ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0116720000፣ 0920169144 እና 0913379489 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ

Save Tender