የተለያዩ የስልጠና መሳሪያዎች፣ ብረታብረት፣ ጽ/መሣሪያ፣ አይሲቲ፣ ደንብ ልብስና ጫማ እና የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ (10 ሎት፣ 01/2019) - የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለኮሌጁ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ብረታብረቶችና የብረታብረት ሥራ መሳሪያዎች
- የእንስሳት ጤና ሳይንስ ሥልጠና መሣሪያዎች
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽ/መሣሪያዎች
- የአይሲቲ ሥልጠና ቁሳቁሶች
- የሠራተኞች ደንብ ልብስና ጫማዎች
- የጋርመንት ሥልጠና መሳሪያ
- የእንስሳት እርባታ ሥልጠና መሳሪያ
- የአፀዋት ሳይንስ ስልጠና መሳሪያ
- የቢዩልዲንግ ኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ሥልጠና መሳሪያ
- የቢሮ ፈርኒቸርን
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚሁ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድና የዘመኑን የስራ ግብር አጠናቀዉ የከፈሉበት ማስረጃ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የንግድ መለያ ቁጥር/Tin number/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በደ/ምዕ/ኢ/ት/ህ/ክ/መ/ ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ከሚገኘዉ ከማሻ ኮ/ኢ/ን/ኮሌጅ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለት/ት መሳሪያዎች ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር/፣ ለደንብ ልብስና ጫማዎች ብር 3000/ሦስት ሺህ ብር/፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎችና ጽ/መሳሪያዎች 3000/ሦስት ሺህ ብር/ እና ለፈርኒቸር 5000.00/ አምስት ሺህ ብር/ CPO ከታወቀ ባንክ አስይዘው ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
- 16ኛዉ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው 10% በCPO ወይም በጥሬ በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው እቃዉን በራሱ ወጪ ዕቃዎችን አጓጉዞ እስከ ኮሌጁ ግቢ በማቅረብ ማስረከብ አለበት።
- [ስለ ናሙና የሚገልጸው ክፍል በፎቶው በግልጽ አይነበብም]
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910095932/0925320744 መደወል ይቻላል።
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Masha Construction & Industrial College seeks suppliers for training equipment and materials across 10 lots: metalwork tools, animal health and science training equipment, ICT materials, consumables/stationery, staff uniforms and shoes, garment training tools, building electrical installation tools, and office furniture. Bidders need a renewed license, tax and VAT registration, and TIN.
