Tender Detail

Tender Details

  • Company ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አስኮ እያሱ ፀበል በአከሱም አዳራሽ 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 2 73 17 69
  • Website
  • Deadline27 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-27 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

 

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1.     በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ጨረታ ለመወደደር የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

2.     የ/VAT/ ተመዝጋቢ ወይም የR ኮድ የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኝ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

3.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡00 በቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት አንድ መቶ (100) ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

5.     ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

6.     የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

7.     ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን በመሙላት ኦርጅና ፋይናንሻል፣ ቴክኒካል ሰነድ እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማግልፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.     ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው።

9.     ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል።

10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ቃሌ ቅድመ 1ኛ፡ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አስኮ እያሱ ፀበል በአክሱም አዳራሽ 400 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 2 73 17 69 በጉ/ክ/ከ/ወ/05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE