Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ/ና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት፣ ማስጠገን እና ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ/ና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2984/002/2018

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ/ና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት፣ ማስጠገን እና ማሰራት ይፈልጋል።

•        ሎት-1 አላቂ የቢሮ እቃዎች እና አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

•        ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች

•        ሎት-3 የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ አላቂ እቃዎች

•        ሎት-4 ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች

•        ሎት-5 ለአላቂ የህክምና እቃዎች

•        ሎት-6 የኮፒ ማሽን እና የተለያዩ ጥገናዎች

•        ሎት-7 ልዩ ልዩ አላቂ እቃዎች

•        ሎት-8 የጭነት አገልግሎት ግዥ

ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች ላይ ለምትሳተፉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘረውን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ይሆናል።

1.     በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

2.     የአቅራቢዎች ምዝገባ (www.egp.ppa.gov.et ) ላይ የተመዘገበ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤

3.     ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሠዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር ብቻ /ሁለት መቶ ብር/ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 በመክፈል ከግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር R-18 ደግሞ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ሥር በተቀመጠው ዝርዝር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ ተጫራቾች መረጃቸውን በአራት ካኪ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) በማድረግ ፋይናሻል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ኦርጅናል እና የፋይናሻልና የቴክኒካልን ለየብቻው ኮፒ (ቅጅ) ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

 

ሎት

የእቃው /የስራው/ ዓይነት

ከአጠቃላይ በጀት የተወሰደው መጠን በ%

ለየሎቱ የሚያሲዘው ማስከበሪያ (CPO) መጠን

1

አላቂ የቢሮ እቃዎች እና አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

1%

3,900 ብር

2

የጽዳት ዕቃዎች

2%

2,000 ብር

3

የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ አላቂ እቃዎች

1%

7,600 ብር

4

ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች

0.5%

5,500 ብር

5

ለአላቂ የህክምና እቃዎች

0.5%

1,000 ብር

6

የኮፒ ማሽን እና የተለያዩ ጥገናዎች

1%

2,000 ብር

7

ልዩ ልዩ አላቂ እቃዎች

2%

1,500 ብር

8

የጭነት አገልግሎት ግዥ

1.5%

1,500 ብር

 

5.     ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ /specification/ ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ በየገፁ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ ግዴታ ነው።

6.     ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የራሳችሁን እሴት ያልጨመራቹ እና አምራች ያልሆናቹ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ 200.00 ብር ብቻ /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ሲፒኦ በማስያዝ መወዳደር ትችላላቹ አምራች የሆናቹ ከአደራጃቹ ተቋም የትምህርት ቤታችንን ስም እና የጨረታውን ቁጥር ጠቅሰው በመጻፍ መሳተፍ ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ (CPO) 10% ያስይዛሉ፤ እንዲሁም አታችመንት ደረሰኝ QR ኮድ ያለው መሆን ይኖርበታል።

8.     የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን 04፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ሠዓት በት/ቤቱ ቤተ መፅሃፍት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያግደውም እንዲሁም የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው /ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሀገር አቀፍ ክብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

9.     ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ላይ ናሙናዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።

10. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት አይኖረውም።

11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ግዴታ አለበት።

12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ሎት 6ን በተመለከተ ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡት ለስራዎቹ የሚያገለግሉ እቃዎችን እና አጠቃላይ የጉልበት ዋጋን ጨምሮ ነው እንዲሁም ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት ስራዎቹን በአካል በመቅረብ መመልከት ግዴታ ሆኖ ማየታቸውን የሚያረጋግጥ ፊርማ ማኖር ይኖርባቸውል።

 

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት ፅ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር የአንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት አስኮ ሊዝ መንደር ቆዳ ሜዳ አጠገብ ይገኛል (የቀድሞ ረታ ት/ቤት) ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁጥር 011-2- 73-14-41 ወይም 0112-73-08-02 ወይም 011-73-19-38

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአስኮ አዲስ ሰፈር አንደኛ/ና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

Save Tender