በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለክ/ከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የጨረታ መመሪያ፡-
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) Tin ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በአቅራቢዎች ዝርዘር የተመዘገቡና ግብር መከፈሉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
2. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
4. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰአት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
7. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡ ተጫራቾች የቀረበውን እስፔስፊኬሽን በመተው ዋጋ ሞልተው ቢገኙ ባቀረብነው እስፔስፊኬሽን እንደተሞላ ሆኖ ይወሰዳል፡፡
8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ናሙና የተጠየቀባቸውን እቃዎች እንደ የደንብ ልብስ፡ ኤሌክትሮኒክስ እና የጽዳት እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በ10 (አስር) ቀን ውስጥ ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው የጨረታው ውጤት ተገልጾ እስከ 5 (አምስት)ቀን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ቀን በኋላ የመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
11. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ለሁሉም ዕቃዎች ቫትን (VAT) ጨምሮ መሙላት እና አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን የእቃ አይነቶች እስከ መስሪያ ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ ፡፡
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
