Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address ልዩ ቦታ ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline11 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-11 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Catering And Cafeteria Services

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1.     ሎት 3 የደንብ ልብስ /ሲፒኦ ማስያዣ የጠቅላላውን ዋጋ 1%

2.     ሎት 4 ለሰራተኞች መገልገያ የሚሆን ካፍቴሪያ /ሲፒኦ ማስያዣ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1.     የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የገበሩ፣

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

3.     በየሎቱ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

6.     ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተብ ማድረግ፣ ስርዝ ድልዝ የሌለው ዋጋ መሙላትና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን ከሚያስገቡት ዶክመንት ጋር በማያያዝ ተመላሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

7.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.     አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- ለናሙና ማስቀመጫ በቂ ቦታ ስለሌለን የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ በ1 ወር ውስጥ ያቀረባችሁትን ናሙና እንድትረከቡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው የንብረት ብክነት እና ብልሽት ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

አድራሻ፡- አ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታ ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት

Save Tender

በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ስፖርት ምክር ቤት ግዥ ቡድን በግልፅ ጨረታ ቁጥር 02/2019 ዓ.ም ከዚህ በታች ለተ...

READ MORE
በድጋሚ የወጣ የፅዳት፣ የቢሮ እቃዎችና ፅህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስና ስፌት፣ ጎማ፣ የኮምፒውተር ጥገና እና የዲኮር ኪራይ ጨረታ (7 ሎት) - በጉለሌ ክ/ከተ...

READ MORE