Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ቁጥር 002/2018 ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ የጥገና እቃዎች እና ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ቁጥር 002/2018 ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ የጥገና እቃዎች እና ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

በዚህ መሰረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

1.     በዘርፋ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገባችሁ

3.     የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ወይም የዘመኑን ግብር ከፋይ የሆናችሁ

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ

5.     ጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ብር /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ

6.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር

ሎት                                                                      የገንዘብ መጠን

1. ሎት 1 የደንብ ልብስ ----------------------------------------------------- 2,000.00

2. ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ---------------------------------------------- 3,000.00

3. ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች ------------------------------------------ 10,000.00

4. ሎት 4 የፅዳት እቃዎች --------------------------------------------------- 2,000.00

5. ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ---------------------------------------------- 10,000.00

6. ሎት 6 የጥገና እቃዎች ---------------------------------------------------- 2,000.00

7. ሎት 7 የጀኔሬተር ጥገና --------------------------------------------------- 5,000.00

8. ሎት 8 የላውንደሪ ማሽን ጥገና ------------------------------------------- 10,000.00

9. ሎት 9 የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት ---------------------------------------------- 5,000.00

10. ሎት 10 የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፋባቸው መድሐኒቶች ማስወድ ---- 10,000.00

 

በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ የተመሰከረለት CPO እና BID BOND ማስያዝ የሚችል ብቻ

7.     ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ VAT 15% ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 227 በመግዛት በታሸገ ፓስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃዎች ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ውስጥ ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው።

11. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ማቅረብ ለማይችሉት በፎቶ ማቅረብ ይኖርበታል።

12. ፋይናሻል ኦርጅናል ፋይናሻል ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።

13. ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ሰነድ ላይ መመልከት ይችላሉ።

 

አድራሻ :- ከ6ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111261509/0111261961 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ

Save Tender