የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽሕፈት ቤት /ጅማ/
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
• ሎት 1 የደንብ ልብሶች
• ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች
• ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
• ሎት 4 የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
• ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች
1) በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፣ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2) ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
3) ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በሪጅን ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4) ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
5) ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6) ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
7) ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን ዕቃዎች ጽ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ጅማ ከተማ አባ ጅፋር አደባባይ (አራቱ አንበሳ) የጅማ ከተማ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ያለው አዲሱ የሪጅን ጽ/ቤቱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ:- 09 17 28 36 17 ወይም 09 17 87 80 57 መደወል ይቻላል፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽሕፈት ቤት /ጅማ/
