Tender Detail


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ብርሃንና ሰላም አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ብርሃንና ሰላም አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን

ሎት 1. ደንብ ልብስ፣ ሎት 3. የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 4. የሕክምና ዕቃዎች ፣ ሎት 5. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 6. የተለያዩ መሣሪያዎች፣ ሎት 7. የማሽነሪ መሣሪያዎች፣ ሎት 8. ልዩ ልዩ ውጤቶች፣ ሎት 9. የጥገና ዕቃዎች፣ ሎት 10. ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 11. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1.     የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።

2.     የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያለው።

3.     የግብር ክሪላንስ ያለው᎓᎓

4.     የአቅራቢነት ሊስት መመዝገባቸውን/በዌብ ሳይት ማረጋገጥ የሚችል፡፡

5.     የVAT መመዝገባቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

6.     የጥቃቅንና አነስተኛ በሚያመርቱት ምርት የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡

7.     የጨረታ ማስከበሪያ የጥቃቅን የአምራችነት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡

ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችል።

1.     ሎት 1 የደንብ ልብስ ሲፒኦ ብር -7,480.00 /ሰባት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ ብር/ ብቻ (2%)

2.     ሎት 3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሲፒኦ ብር - 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ (2%)

3.     ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሲፒኦ -8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ (2%)

4.     ሎት 6 የሕክምና ዕቃዎች ሲፒኦ ብር - 1,210.00 /አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስር ብር ብቻ (2%)

5.     ሎት 7 የፅዳት ዕቃዎች ሲፒኦ ብር - 3,725.00 /ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ብር ብቻ (2%)

6.     ሎት 8 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ ሲፒኦ ብር - 14,128.00 /አስራ አራት ሺ አንድ መቶ ሃያ ስምንት ብር ብቻ (2%)

7.     ሎት 9 የማሸነሪ መሣሪያዎች ዕድሳት ሲፒኦ ብር- 1,500.00 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ ብቻ (2%)

8.     ሎት 10 ልዩ ልዩ የሕንፃ ጥገና ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 1,943.00 /አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ብር ብቻ (2%)

9.     ሎት 11 ቋሚ ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 4,290.00 ብር (አራት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ብር ብቻ (2%) ጠቅላላ ድምር 50,276.00 /ሀምሳ ሺ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ብር/ ብቻ

10. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 07 እየቀረቡ መግዛት ይችላል፡፡

11.ተጫራች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

12. ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በ 5፡00/ አምስት ሰዓት/ ይከፈታል፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

13. ተጫራቾች ያሸነፉበት ዋና ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

14. ተጫራቾች ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የሚቀርብባቸው እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን (Specification) መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

15. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት እቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።

16. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነሰም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍl ከተማ ወረዳ 03 የብርሃንና ሰላም አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከአማኑኤል ቶታል ወረድ ብሎ ይገኛል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0112736093/0112736094/0112132493

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ብርሃንና ሰላም አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

Save Tender