Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሠራተኞች ሁለገብ የሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ የቤት ፍርስራሽ ቆርቆሮዎች ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች ሁለገብ የሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር


 

ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግጨ-001/18

 

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሠራተኞች ሁለገብ የሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ የቤት ፍርስራሽ ቆርቆሮዎች ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ግቢ ውስጥ በመገኘት የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት ይችላል፣
  2. እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታው አፈፃፀም የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር ቢሮ ቁጥር 80 ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሠነዱን መግዛት ይችላል፣
  3. እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. የጨረታው ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ከገዛው ዋጋ ጋር የሚደመርለት ሲሆን በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ንብረት ዋጋ ከፍለው በ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን ማንሳት አለባቸው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከፍለው ንብረቶቹን ማንሳት ካልቻሉ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር ገቢ ይሆናል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- የስልክ ቁጥር 0965172383 ወይም 0946728918 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች ሁለገብ የሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማኅበር

 

Save Tender