Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address አዲሱ ገበያ ወደ ቀጨኔ በሚያስኬደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሐምሌ 19/67 ት/ቤት አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline31 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000 /ሃያ ሺ ብር/
  • opening date2026-01-01 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ግቢ ውስጥ የሚኘው የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የተለያዩ ምግቦችን የተለያዩ ትኩስ ነገሮችን እና የቀዝቃዛ መጠጦችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን በተመጣጣኝ የመዝናኛ ኪራይ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት


 

የመዝናኛ ክበብ ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ግቢ ውስጥ የሚኘው የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የተለያዩ ምግቦችን የተለያዩ ትኩስ ነገሮችን እና የቀዝቃዛ መጠጦችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን በተመጣጣኝ የመዝናኛ ኪራይ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የሰራተኛ መዝናኛ ክበቡ የሚገኝበት ቦታ፡- ጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ግቢ ውስጥ

  1. ተወዳዳሪዎች ሲወዳደሩ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በቀረበው የዋጋ እና መጠን ዝርዝር ትይዩ ባለው የተወዳዳሪዎች የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ መሙላት አለባቸው።
  2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የቫት /VAT/ የሆናቸው።
  3. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም።
  4. አሸናፊው ተወዳዳሪው ሁሉንም ለስራው የሚያስፈልገው ማቴሪያሎች በራሱ ገዝተው ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  5. ተወዳዳሪው አሸናፊ ሆኖ ቢገኝ ከመንግስት ጋር ስለሚኖረው የህጋዊነት መሰረት ማለትም እንደንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ ቲን ቁጥር ማውጣት እንዲሁም የደረሰኝ ማሳተምም ይሁን የደረሰኝ ማሽን መጠቀምን አስመልክቶ በአሸናፊ ወጪ ይፈፀማል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠው ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. መዝናኛ ክበቡ አቅሙ በፈቀደ መጠን የውሃ፤ የመብራት እና የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ቤት በነፃ ለአሸናፊው ይሰጣል።
  9. አሸናፊው አካል ስራ ሲጀምር መዝናኛ ክበቡን በጥራትና በውል በሚታሰረው አግባብ መሰረት በእንክብካቤ መያዝ ይጠበቅበታል።
  10. ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነው ስራ ሲጀምሩ በአስተዳደሩ ግቢ የሚሰሩ መንግስት ሰራተኞች ፣አመራሮች የኮንትራት ሰራተኞች፣ የገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኞችን እንደእስታፍ አገልግሎት ይሰጣል።
  11. ዋጋ ከሞሉ በኋላ ሁሉም ተወዳዳሪዎች በእያንዳንዱ ሰነድ ገጽ ላይ ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎች መፈረም አለባቸው።
  12. አሸናፊው አካል ለስራ የሚያስገባቸው እቃዎች ሲለቅ ቢፈልግ እዳ እስከሌለበት ድረስ ይዞ መሄድ ይችላል እዳ ካለበት ግን ለእዳው ማካካሻ እንዲውል ይደረጋል አፈፃፀሙ ግን በውል ውስጥ የማካተት ነው።
  13. መዝናኛ ክበቡ የሚውል በግዥም ይሁን በድጋፍ እያሟላ ሲሄድ የቢሮ ኪራዩ ላይ የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ ይችላል።
  14. የጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10 ቀን በእለቱ 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ባይገኘም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል። ነገር ግን የመንግስት ስራ የማይኖርበት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  15. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸውን በደብዳቤ በተገለጸላቸው 7 የቅሬታ ቀናት ካለቀ በኋላ ከ8-15 ባሉት ቀናት ውስጥ ውል መዋዋል አለባቸው።
  16. መ/ቤቱ ወረዳው ጨረታው በከፊልም ይሁን ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር አዲሱ ገበያ ወደ ቀጨኔ በሚያስኬደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሐምሌ 19/67 ት/ቤት አጠገብ

 

የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE