Tender Detail

Tender Details


ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወንድማማች አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወንድማማች አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት


 

ለሁለተኛ ዙር የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወንድማማች አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የትምህርት እቃዎች
  2. የደንብ ልብስ
  3. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  4. አላቂ የፅዳት እቃዎች
  5. ቆሎ እና ኩኪስ
  6. የደንብ ልብስ ማሰፊያ

በዚህ መሠረት በጨረታው መሣተፍ ለሚፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር / ተከታታይ የሥራ ቀናት በወንድማማች የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 4 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙናውን ካላቀረቡ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው ሰነዱ ኮፒና ኦርጅናሉ ብሎ በመለየት በታሸገ ኢንቨሎፕ በተለያዩ ፖስታ አሸገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣበት በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ በ4፡45 ሰዓት በት/ቤቱ የሰው ኃይል ቢሮ ይከፈታል እለቱ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይሆናል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ዋጋ ሲያቀርቡ እስከ ቫቱ እንዲያቀርቡ፡፡
  13. አነስተኛና ጥቃቅን የተደራጃችሁ አቅራቢዎች ካላችሁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፡፡
  14. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ ማብራሪያ፡-

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ቡልጋሪያ ከቀድሞው በግ ተራ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቢይ ሜዳ ኮንዶሚኒየም አጠገብ

የስልክ ቁጥር፡- 0114164212/0114705897

የመ/ሣ/ቁ፡- 6388 አዲስ አበባ

 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወንድማማች አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጥቅል 1 -- Kitchen Material ans hand tools (የኩሽ...

READ MORE
በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE