በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር: 004/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ - የተሽከርካሪዎች ጥገናና ሰርቪስ (ጋራዥ)
- ሎት ሁለት - የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት ሶስት - Indoor SMD LED display screen and digital signage kioski
- ሎት አራት - AC
- ሎት አምስት - የሚዲያ ጭውውት
- ሎት ስድስት - የሬዲዮ አየር ሰዓት
- ሎት ስምንት - የጽሕፈት መሣሪያዎች
- ሎት ዘጠኝ - የወንበር እና ጠረጴዛ ጨርቅ
- ሎት አስር - መጋረጃ
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ™ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር "አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማኅተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎኘ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) በ4፡00 በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 10,000.00፣ ለሎት ሁለት 2%፣ ለሎት ሦስት 2%፤ ለሎት አራት 2%፤ ለሎት አምስት 10,000.00፤ ለሎት ስድስት 10,000.00፤ ለሎት ሰባት 2%፤ ለሎት ስምንት 2%፤ ለሎት ዘጠኝ 2% ፤ ለሎት አስር 2%፣ የሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ C.P.O ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። C.P.O መሥራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቶች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ስዓት የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእ.ታ ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እታ /ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሽነፋባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0115 57 57 42/0115 57 57 19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
