በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ ወረዳ የመጀ/ደ/ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት እቃዎች፣ የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ ህትመት፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ኤስፔር ፓርት፣ ፈርኒቸር እና የመንግስት ሰራተኛ ደንብ ልብስ በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ ወረዳ የመጀ/ደ/ሆስፒታል
የአገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ ወረዳ የመጀ/ደ/ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት እቃዎች፣ የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ ህትመት፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ኤስፔር ፓርት፣ ፈርኒቸር እና የመንግስት ሰራተኛ ደንብ ልብስ በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው።
- ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ እና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. ቁ. 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በሁለት አርጅናልና ኮፒ ብሎ ማቅረብ አለባቸው።
- የሁሉንም የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተቋሙ ከአወጣው ስፔስፍኬሽን ውጭ በራሱ ጊዜ ስፔስፍኬሽን የጨመረና የቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ከ08/04/2018 ዓ.ም እስከ 22/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/የመ/ደ/ሆስፒታል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን ማለትም 23/04/2018 ዓ.ም ከ2፡00 እስከ 5፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/የመጀ/ደሆስፒታል በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ ውድድሩ በሎት /በጠቅላላ ድምር/ ስለሆነ የሚሞሉት የጨረታ ሰነድ አንዱም ዕቃ ሳይሞሉ ከቀሩ ከጨረታው ከውድድሩ/ ውድቅ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነድ ላይ ከአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆነ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /በሲፒ.ኦ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸ ቀን ጀምሮ በ8 ቀን ውስጥ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ ወረዳ የመጀ/ደ/ሆስፒታል
