Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለባቲ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለባቲ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ምድብ 1፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ምድብ 2፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች ምድብ 3 ኤሌክትሮኒክስ ምድብ 4፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፈርኒቸር/ ምድብ 5፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ምድብ 6፣ የውሃ መለዋወጫ እቃዎች ምድብ 7፣ ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች ምድብ 8፣ የግንባታ እቃ ምድብ 9፣ የመንገድ ቆረጣ ከማመድ እስከ ገርፋ ኡረኔ ቀበሌ ያለውን መንገድ ለማስጠገን /ለማስቆረጥ/ 9 ኪ.ሜ 130 ሰዓት፣ እንዲሁም ከካራ እስከ ዳመቶ ያለውን መንገድ አዲስ መንገድ /ለማስቆረጥ/ 15ኪ/ሜ 295 ሰዓት የሚያገለግል የማሽን /ዶዘር/ ኪራይ የዶዘር ሞዴል D8R 2015 እና ከዛ በላይ የፈረስ ጉልበት 300 እና ከዛ በላይ የሆነ በሰአት ለማሠራት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN/ ያላቸው።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የገንዘብ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጂዎች ማለትም ኮፒና ኦርጂናል በማለት በጥንቃቄ በታሸነ ኤንቨሎፕ ባቲ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው::
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት የጨረታ አይነት ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ምድብ 1፣ ብር 5,000 ምድብ 2፣ ብር 1500 ምድብ 3፣ ብር 2,000 ምድብ 4፣ ብር 2,000 ምድብ 5፣ ብር 1,500 ምድብ 6 ፣ ብር 2,000 ምድብ 7፣ ብር 500 ምድብ 8፣ ብር 3,000 ምድብ 9፣ ለእያንዳንዱ ብር 30,000 በመ/ቤታችን ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም የጨረታ ማስከበሪያ / ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ከምድብ 1- ምድብ 8 ድረስ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ /ብር እንዲሁም ምድብ 9 ለእያንዳንዱ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ከምድብ1- ምድብ 8 ድረስ ያሉትን ሰነዱ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከ14/4/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/04/2018 ዓ.ም ድረስ አየር ላይ ይውላል፡፡ በ20/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. እንዲሁም ምድብ 9 የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ከ04/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 24/4/2018 ዓ.ም ድረስ አየር ላይ ይውላል በ27/04/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ስም፣ ማህተምና ፊርማ አሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው የሚለየው በጥቅል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  12. ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ የግ/ፋ ን አስ/ደ/የሥራ ሂደት በአካል ቀርበው ወይም

 

በስ.ቁ 033 5532123 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender