Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የደንብ ልብስ እና የጥገና ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ ጤና ጣቢያ


 

የ3ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የደንብ ልብስ እና የጥገና ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።

በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
  • በየሎት 1, የመድሀኒትና ለላብራቶሪ ሪኤጀንቶች 10,000 ብር
  • 2 የሕክምና መሳሪያዎች- 10,000 ብር
  • 3 የጥገና ስራዎች- 20,000 ብር
  • 4 የፅዳት ዕቃዎች- 1,000 ብር
  • 5 የደንብ ልብስ - 1,000 ብር
  • 6 የደንብ ልብስ ስፌት - 1000 ብር

በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን በመገኘት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  3. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
  5. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 የስራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል።
  6. አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
  7. ጤና ጣቢያው የአቅርቦት ዝርዝር (ስፔስፍኬሽን) በሚጠይቁ አቅርቦቶች ላይ ባወጣው መሰረት ተጫራቾች ካታሎግን ጨምሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የጨረታም ሆነ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አሸነፋችሁም አላሸነፋችሁም ከ6ወር በፊት መውሰድ ይኖርባችዋል ከ 6 ወር በኋላ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን።
  9. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡- 011 893 29 82/011 667 42 37

 

በየካ ክ/ከተማ የየካ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት

 

Save Tender

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB /05/2019 ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል የቅያስ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት አመት በውል አስሮ ማሰራት...

READ MORE
በድጋሚ የወጣ የፅዳት፣ የቢሮ እቃዎችና ፅህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስና ስፌት፣ ጎማ፣ የኮምፒውተር ጥገና እና የዲኮር ኪራይ ጨረታ (7 ሎት) - በጉለሌ ክ/ከተ...

READ MORE