Tender Detail

Tender Details

  • Company የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እና ትምህርት ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address መገናኛ ከ22 ታክሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 668 41 08
  • Website
  • Deadline23 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-23 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በጋራ የምንገለገልበት የመንግስት ሰራተኞች መዝናኛ ክበብ በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::

የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እና ትምህርት ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በጋራ የምንገለገልበት የመንግስት ሰራተኞች መዝናኛ ክበብ በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፣
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፣
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በአንድ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል መግለጫው እና ፋይናንሺያል ዋጋው በዝርዝር ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒውን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ ቀን ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 502 ማስገባት አለባቸው።
  6. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል፣
  7. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 መውሰድ ይችላሉ ፣
  9. ቅርንጫፍ /ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉት ለስራው የሚያስፈልጉ እቃዎች ለአብነት ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ የትኩስ መጠጥ ማሽኖች፣ የምግብ ማብሰያ እቃዎችና ወዘተ አሟልተው ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ለሆኑ ብቻ ነው።

 

በመ/ቤቱ በኩል በነፃ የምናቀርባቸው

  • የቤት ኪራይ በነፃ
  • የኤሌክትሪክ ክፍያ በነፃ
  • የውሃ አገልግሎት በነፃ የምናቀርብ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

 

አድራሻ፡-

  • መገናኛ ከ22 ታክሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 ነው:: ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የስልክ ቁጥር 011 668 41 08 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።

 

የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እና ትምህርት ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE