በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ የመ/ሜዳ/ፖ/ቴ/ ኮሌጁ በ2018 ዓ.ም ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሰልጠኛ ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክኒክና ሙያት ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የመሐል ሜዳ /ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ የመ/ሜዳ/ፖ/ቴ/ ኮሌጁ በ2018 ዓ.ም ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማሰልጠኛ ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ሎት1 የጽህፈት መሳሪያ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት2 የጽዳት እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት3 የህንጻ መሳሪያ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት4 የኮምፒውተርና ተዛማጅ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት5 የመብራትና ተጓዳኝ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎተ6 የብትን ጨርቅ እና ክራክር ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት7 የመኪና እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ሎት8 የእንሰሳት ጤና መድሃኒትእና የህክምና እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት9 የተዘጋጁ ደንብ ልብስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ሎት10 የጫማ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ሎት11 የቤትና የቢሮ እቃ ህጋዊ ንግድ በፍቃድ እና ሎት12 ሳይክልና ጎማ ህጋዊ ንግድ በፍቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሰ/ሸ/ዞ/መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በመ/ሜዳ/ፖ/ቴ/ኮጅ ቢሮ ቁጥር 6 ቀርቦ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመግዛት የጨረታው ተሳታፊ መሆን እንደሚችል እንገልጻለን።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች፡-
- በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ነምበር፣
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ 1% ማስያዝ አለባቸው፣
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፣
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት መረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን 27/03/2018 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ15ኛው ቀን ልክ ከቀኑ 11፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል። ተጫራቾች ይኸ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የዋጋ ማቅረቢያውን በመ/ሜዳ/ፖ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ቀርቦ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11/04/2018ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ12/04/2018 ዓ.ም ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ ባሉበት ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን በበኣላት ቀን ከዋለ የጨረታው መክፈቻ ቀኑ በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋ ማቅረቢያ ፖስታውን በሰ/ሸዋ ዞን በመ/ሜዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 ቀርቦ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ኮሌጁ የተጠቀሱትን ማቴሪያሎች እንደ አስፈላጊነቱ በምዛዣ ወይም በሎት ሊገዛ ይችላል።
- በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ ማቅረቢያ ከተጠናቀቀ በኃላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ማቴሪያሎች የማጓጓዣ ወጪ እራሳቸው ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ውጤቱ ከተገለፀበት 10 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በማሟላት መዋዋል አለበት።
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ10 ቀናት ውስጥ ውለታ ካልፈጸመ የአስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ካስፈለጋቸው የመ/ሜዳ ቴ/ሙ/ትም/ስልጠና ኮሌጅ የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0116 850 413 / 0930 648 548 / 0920 855 182 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክኒክና ሙያት ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የመሐል ሜዳ /ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ
