በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለመምሪያው እና በስሩ ለሚገኙት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚውል ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ/ም
ኮ/ቀ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለመምሪያው እና በስሩ ለሚገኙት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚውል ዕቃዎች ለመግዛት የወጣ ጨረታ ነው፡-
- ሎት 1 የቋሚ እቃዎች
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3 የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 4 የፅዳት ሠራተኞች አልባሳት
- ሎት 5 የፉርኖ ዱቄት
- ሎት 6 የተሽከርካሪ ጎማ
- ሎት 7 የእስረኛ ቀለብ
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው።
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች 1-4 የተጠቀሱትን የንግድ ፍቃድ፣ የቫት የቲን መለያ ቁጥርና የአቅራቢነት ምዝገባ መረጃዎችን የጨረታ ዶክመንት ሲያስገቡ ኦርጅናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው በመሆኑም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ ፋ/ግዥ/አስ/ር ዲቪዚዮን 4ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የእቃ መጠን እያንዳንዱ ሎት1 10,000 ሎት2 4,000 ሎት3 3,000 ሎት 4 5,000 ሎት 5 20,000 ሎት 6 1,500 እና ሎት 7 3,000 ሲሆን ከአንድ ሎት በላይ የሚጫረቱት ተጫራቾች የሎቶቹ ድምር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.አ በኮ/ቀ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቹዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያዩ ፖስታ በማስገባት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ/ግዥ/ዲቪዚዮን 4ኛ ፎቅ በማቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኮ/ቀ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ /ግዥ/ዲቪዚዮን 4ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች በእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- በተሰጠው የጨረታ ሰነድ ብቻ ሞልቶ ማቅረብ ይገባዋል።
- ሎት 2፣ 3፣ 4፣ 5 እና 7 ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሎት /ዕቃዎች አማራጭ ዋጋ ማስቀመጥ አይቻልም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከጦር ሃይሎች በስተግራ ቀለበት መንገድ ሲወርዱ የቀድሞው ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ሳይደርሱ
ስልክ ቁጥር፡- 011-3-20-44-46/011-371-77-41 ደውለው መረዳት ይችላል።
በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
