በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የተሽከርካሪ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የተሽከርካሪ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ /Specification/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 / አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ /CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሠረት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀኖች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ስነ-ስርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0473351027/0473351278
የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሚዛን አማን
