ድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
የሸቀጥ ግዥ የጨረታ
ማስታወቂያ (ቁጥር 003/2018)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ፓስታ CES 1055፡2022፣ 2. ሩዝ ES ISO 7301:2022፣ 3. ከሸንኮራ አገዳ የተመረተ ስኳር ICUMSA 45 (SUGAR CANE) ፣ 4. የተለያየ መጠን ያላቸው የብርድ ልብስ ምርቶች (ES3840:2015) 5. የተለያየ መጠን ያላቸው ፎጣዎች፣ 6. የተለያየ መጠን ያላቸው የልብስ ማጠቢያ ሳሙናዎች CES42:2021፣ 7. የቆርቆሮና ግድግዳ ሚስማር (CES33:2023)፣ 8. የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 21:2024) 9. የተለያየ መጠን ያለው ፈሳሽ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና (CES268:2020) በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለሩዝ እና ስኳር አምራች ወይም አስመጭና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ምርቶች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0111-28-15-29
www.eiide.com.et.com.et
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
