Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ
  • Address ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security5,000 (አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ


 

2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2018

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት-1. የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ አገልግሎት

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.go.et online ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚረጋገጥ ይሆናል ፡፡
  6. ተጫራቶች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት፡፡ ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጪ ይሆናል ፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቶች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  10. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
  11. ቀጣዩ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተራ ቁጥር 10 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈፃሚ ይደረጋል ፡፡
  12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  13. በጥቃቅን የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበት ዘርፍ በግልፀ የተቀመጠና በምግብ ሥራ ላይ የተሰማራ መሆኑን የሚገልፅና ደብዳቤውን ለመፈረም ሥልጣን በተሠጠው አካል የተፈረመ ስልክ ቁጥር ያለው እና የተደራጀው የሚሰራበት ቦታ ተጠቅሶ የዋስትና ደብዳቤው ለጨረታ ማስከበሪያና ለውል አለባቸው።
  14. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና አገልግሎት ለመስጠት በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለመጨረስ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
  16. ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ከ7 ቀን በኋላ ውል ተዋውለው ሥራ መጀመር አለባቸው፡፡
  17. አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኋላ ጤና ጣቢያ ያስቀመጣቸውን የምግብና የመጠጥ አይነቶችን በሙሉ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ከዚህ በፊት የካፍቴሪያ /የምግብ/ ሥራ አገልግሎት ሰርቶ የሚያውቅና ልምድ መኖሩን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  20. ወርሃዊ የመብራት እና የኤሌክትሪክ ፍጆታ በግዥ ፈፃሚው ተቋም ይሸፈናል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- የዋጋ መሙያ ክፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የምግብ እና የመጠጥ አይነቶች በሙሉ አቅራቢው ድርጅት ዋጋ መሙላት ግዴታ አለበት፡፡

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ

Save Tender