Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ሥልጣን ጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0116-676529
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

አዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የካፍቴሪያ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ሥልጣን ጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NCB/GOV/AAWSA/GS/002/2018

አዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የካፍቴሪያ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1 ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣ የዘመኑን ግብርየከፈለ እና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የምዝገባ ምስከርወረቀት፣ የግብር _ ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የተ.ጨ.እ ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡

2. በሆቴል፤በካፍቴሪያ ወይም ተመሳሳይ ዘርፍ የስራ ልምድ ያለው እና በዚህ ስራ ዘርፍ ባለፉት ሶስት ዓመት ቢያንስ አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፡፡

3. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 404 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቢሮ ቁጥር 404 በመምጣት ለዚህ ዓላማ በተዘጋጅው ሳጥን በታሸገ ፖስታ ወይም ኤንቨሎፕ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5. ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል፡፡

6. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ውክልና የያዘ ወኪል መሳተፍ ይችላል፡፡

7. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ተጫራቾች ለካፍቴሪያ አገልግሎት የተዘገጀውን ቦታ በተጠቀሰው አድራሻ በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እሰከ አርብ ማየት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው መንገድ ቦሌ ወረዳ 06 ፊት ለፊት ወይም ማማስ ኪችን ጎን አዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 404 ስልክ ቁጥር 0116-676529

በአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ሥልጣን ጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender