የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች በሚሠሩት ፈረቃ የቁርስ፤ የምሣ እና የእራት የምግብ አገልግሎት ይሠጣል። በዚሁ መሠረት በዚህ አገልግሎት የሥራ ልምድና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አወዳድሮ የአንድ ዓመት ኮንትራት በመስጠት ለማሠራት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በግዥ መለያ ቁጥር BTSC/NCB/Serv/08/2018/
የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች በሚሠሩት ፈረቃ የቁርስ፤ የምሣ እና የእራት የምግብ አገልግሎት ይሠጣል። በዚሁ መሠረት በዚህ አገልግሎት የሥራ ልምድና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አወዳድሮ የአንድ ዓመት ኮንትራት በመስጠት ለማሠራት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ (ከዓለም ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 1.3 ኪ.ሜ ላይ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ የድርጅቱ የግዥና አቅርቦት መምሪያ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 10፡30 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ አለበት።
- ጨረታው ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ከጠዋቱ 5፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታው የመክፈቻ ቀን ከአቅም በላይ ሁኔታ ሲገጥም ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 96-67 29 51 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሸገር ከተማ ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከዓለም ገና ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3 ኪ.ሜ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ
ቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር