Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
  • Address በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲየም የክለብ ጽ/ቤቱ ይገኛል። አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-8-81-36-05
  • Website
  • Deadline21 Sep 2026, 3:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/
  • opening dateበዕለቱ 9:30
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Hotel Service Provision , Sport Materials And Sportswear

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን በሆቴል ለመመገብ እና የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገል እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉ ተወዳዳሪዎች እንዲሳተፉ እየጋበዝን፡ -

  1. በየዘርፉ የተሰማራበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. አሸናፊ ድርጅት ለመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን እንዲገዙ እየገለጽን፣ እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ መግለጫውን በማያሻማ መልኩ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በመሙላት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች አርጅናልና ኮፒ በድምሩ 2 ፖስታዎች በሰም በታሸገ እንቭሎፕ ከፊትና ጀርባው ላይ የድርጅቱን ማህተምና የባለቤትነት ፈርማ በማድረግ በእናት ፖስታ ውስጥ ተጨምሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ - ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድን ያካተተ ይሆናል፡፡
  5. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. በጨረታው ያሸነፈ ተወዳዳሪ የባለሙያ አስተያየት ላይ መሠረት በማድረግ ውል ገብተው ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ሁሉም ተጫራች አድራሻውንና ቦታውን እንዲሁም የስልክ ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል፡፡ በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው
  7. የእያንዳንዱ ግዥ መጠን በሽያጭ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
  8. መ/ቤቱ የዕቃው ጥራት በባለሙያና በስፖርተኞች ሲረጋገጥ ብቻ ውል ተዋውሎ ማስቀጠል የሚቻል ይሆናል፡፡
  9. በጨረታው ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለጹ ካሉ እንደ ማስታወቂያ የሚያገለግል ስለሆነ ሁሉም ተጫራች ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል፡፡
  10. ክለብ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
  11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በ6ኛው ቀን ሲሆን በዕለቱ 9፡00 የጨረታ ሳጥን የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የማይገኙ ከሆነ የጽ/ቤቱን ስራ አያስተጓጎልም። የተጫራቹ ተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ስለ ውክልናው ህጋዊነት የሚገልጽ መረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  12. የክለብ ጽ/ቤቱ አድራሻ በአ/ምንጭ ሁለገብ ስታዲዬም የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በ 09009889.62 (0916878422) ይደውሉ፡፡

የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ

✨ messages.ai_summary
Arba Minch City Football Club seeks bidders to provide hotel catering for players and supply sports materials for the 2019 season. Eligible bidders need a valid business license, VAT registration, tax clearance, and a certificate of good performance.
Save Tender