የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም፣
- ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ኮፒ ከቴክኒክ የጨረታ ሰነዳቸውን አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት።
- የወቅቱን የግብር ግዴታ የተወጡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከታክስ ባለስልጣን የተጻፈ ደብዳቤ/Tax Clearance/
- በምግብና መጠጥ ዝግጅት /ምግብ ቤት አገልግሎት ቢያንስ የ2 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ማስረጃ።
- ከሚመለከተው የጤና መስሪያ ቤት የተሰጠ የምግብ ደህንነት እና ንፅህና ማረጋገጫ /Sanitation Certificate/።
- የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ ብር 50000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በ CPO ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመለየት ከታሸጉ በኋላ ሁለቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሚገኘው የግዥ ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ሰነዱ በላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ በሚገኘው አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መ/ቤት በማይከፈል ብር አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0966201857 ወይም 0912333265።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
✨ messages.ai_summary
The Environmental Protection Authority seeks a qualified organization to provide cafeteria services under an open tender. Bidders must submit a valid business license, TIN and VAT certificates, tax clearance, at least 2 years of relevant food service experience, and a health/sanitation certificate.
