በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሠላም በር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመምህራንና ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የውጭ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።
ሠላም ጠር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የመዝናኛ ክበብ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሠላም በር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመምህራንና ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የውጭ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በምግብ ቤት እና መዝናኛ ክበብ የስራ ልምድ ያላችሁ ወይም መስራት የምትፈልጉ ግለሰቦች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሂሳብ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 200 ከፍሎ በመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት (7) የስራ ቀናት እስከ ምሽቱ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለቀረበላችሁ ዝርዝር ሰነድ ላይ የምግብ ዓይቶች ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በግዥ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
- ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት በስምተኛው (8) ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ት/ቤቱ ካቀረበው ዋጋ መሙያ ሰነድ ውጪ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ድልዝ ካለው ለውድድር አይቀርብም፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ የተዘረዘሩ የምግብ፤ የለስላሳ እና የመጠጦች ዋጋ መሞላት አለባቸው። የተዘለለ ማለትም ዋጋ ያልተሞላ ከሆነ ለውድድር አይቀርብም። አሸናፊ ተጫራች የሚሰጠው አገልግሎት እየታየ በየ ሶስት ወሩ ኮንትራቱ ሊታደስለት ወይም ሊቋረጥበት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ያስገቡት ፖስታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 2,000 /ሁለት ሺህ/ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ስፋት———— ካሬ ሜትር ሲሆን በውስጡ ሰፊ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የጀበና ቡና ኮሪደር፣ ኪችን ቤትና እቃ ቤት አሉት፡፡ በአካል ቀርቦ ማየት ይቻላል።
- በተቋሙ ውስጥ ውሀና ሙበራት በመስመር ላይ ካለ የጨረታ አሸናፊው አካል መጠቀም ይችላል። ነገር ግን ውሀና መብራት በመስመር ላይ በማይኖርበት ወቅት ጨረታ አሸናፊው በራሱ መንገድ ውሀና መብራት በማቅረብ አገልግሎ መስጠት ይጠበቅበታል። በተቋሙ ኤሌክትሪክ ለውጪ ሽያጭና እንጀራ እና ዳቦ መጋገር፣ በእስቶቭ የጀበና ቡና ማፍላት፣ ችብስ፣ ሳምቡሳና ኩኪስ መጥበስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፈው የሻይ ማሽን፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ሁለት ቴሌቪዥኖችና ሌሎች የስራ እቃዎች ውል ከመዋዋሉ በፊት ማስገባት አለበት፡፡
- የጨረታ አሽናፊው ለውስጥ ሰራተኞች የሚያቀርብበት የምግብ ዋጋ ተጫራቹ ባቀረበው የምግብ ዋጋ ዝርዝር መሰረት ሲሆን የውስጥ ሰራተኞች አገልግሎቱን ሳያገኙ ምግብ አልቋል ማለት አይቻልም። ነገር ግን ለውጭ ተጠቃሚዎች ተጫራቹ በሚያዋጣው ዋጋ ማቅረብ ይችላል፡፡
- በካፌው ውስጥ ለውጪ ተጠቃሚ ተብሎ ከተወሰነው ቦታ ውጪ የውጪ ተጠቃሚ ማስጠቀም አይችልም። ተቋሙ የቤቱን ኪራይ በነፃ የሚሰጥ ለተዘረዘሩ ምግቦችና መጠጦች የምታስገቡትን የዋጋ ቅናሽ ትኩረት ያደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በጥሬ በወ/10/ትም/ጽ/ቤት በሠላም በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በሚል ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለበት፡፡
- ይህ ማሳሰቢያ የውሉ አካል ሆኖ የሚፀና ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ግብር የከፈሉና ለዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደ ፌደራል ፖሊስ ማስልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፓልት በስተቀኝ በኩል ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ጎን .0112739030
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሠላም ጠር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
