በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአቃ/ቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የግዢ መለያ ቁጥር 01/2018
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በማየት መወዳደር ይችላሉ።
• ሎት 1. 6211/ደንብ ልብስ
• ሎት 2. 6212/አላቂ የቢሮ ዕቃ
• ሎት 3. 6213/ የህትመት ውጤቶች
• ሎት 5. 6215/ የትምህርት ዕቃዎች
• ሎች 6. 6218/ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
• ሎት 7. 6219/ ልዩ ልዩ ዕቃዎች
• ሎት 8. 6313/ ቋሚ ዕቃዎች
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር (TIN NO) ያላቸው፡፡
2. የዘመኑ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት አጠቃላይ ዋጋ መጠን ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁ.9 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በፖስታ በማሸግ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚዘጋው /የሚታሸገው/ ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን (በስራ ቀናት) ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ይሆናል። ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ቀን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን (በስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ይሆናል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት በራሱ ትራንስፖርት ቂሊንጦ 2ተኛ/ደ/ ት/ቤት ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና/ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ፡- መምጣት የማይችሉ ከባድ እቃዎችን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
11. ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል/ ላይ ምንም አይነት ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች እንዳይኖር ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ ምልክት ያለበት ሳምፕል እና የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ ፍሉድ ማስገባት ጨረታውን ውድቅ ያደርጋል፡፡
12. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይኖርባቸዋል።
13. የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% /አስር/ ፐርሰንት ባሸነፉበት ዕቃ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር- 09-11421605-0922024252/ ብለው ይደውሉ፡፡
አድራሻ፡- ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት ያለው ት/ቤት
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
