Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገ/ኢ/ል/ቢሮ በሰ/ወሎ ዞን መምሪያ የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የላስታ ወረዳ ፍርድ ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገ/ኢ/ል/ቢሮ በሰ/ወሎ ዞን መምሪያ የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

 

ምድብ

የንግድ ዘርፍ

ሎት 1

የህትመት አቅርቦት ግዥ

ሎት 2

የጽህፈት መሳሪያ አቅርቦት ግዥ

ሎት 3

የጽዳት ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ

ሎት 4

የተዘጋጁ ደንብ ልብሶች አቅርቦት ግዥ

ሎት 5

የተዘጋጁ ደንብ ጫማዎች አቅርቦት ግዥ

ሎት 6

ያልተዘጋጀ ጣቃ ጨርቅ ወይም ብትን ጨርቅ አቅርቦት ግዥ

ሎት 7

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አቅርቦት ግዥ

 

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሰረት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸውና የሚሞሉት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር የኢት.ብር ለህትመት፣ ለጽ/መሳሪያ፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች/ 50.00 ብር (ሃምሳ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የተዘጋጁ ደንምብ ጫማዎች፣ የተዘጋጁ ደንምብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች እና ያልተዘጋጀ ደንብ ልብስ ጣቃ /ብትን ጨርቅ/ 40 አርባ ብር) ብቻ በመክፈል ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢ/ቁጥር 8 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት የሞሉትን ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታ ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ምክንያት ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይተላለፍ እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በየሎት ምድባቸው በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ውስጥ ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባቸው።
  7. አሸናፊው አካል እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ሲኖርበት ንብረቱ ገቢ የሚደረገው በባለሙያ እየተረጋገጠ ይሆናል።
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የዕቃ አይነቶች ከፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ የሚካሄደው በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት።
  10. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊው መሆኑን ከተገለጸ በኋላ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን 10% በመያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበዎታል።
  12. የተዘጋጁ እና ላልተዘጋጁ የደንምብ ልብሶች እና ደንምብ ጫማ የተሻለ ደረጃ አለው የሚባለውን አቅርቦት ሞልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  13. ፍ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት በማየት ከበጀቱ ጋር በማጣጣም 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም 09 21 96 47 66 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የላስታ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

Save Tender