Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
  • Address 6ኪሎ ወደ ጃልሜዳ መንገድ በሚወስደው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline24 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 19%
  • opening date2025-11-25 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Hospitality Service

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ድርጅቶች ወይም ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ ለ2ኛ ጊዜ አወዳድሮ ማስገባት የሚሰጡ ይፈልጋል፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ድርጅቶች ወይም ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ ለ2ኛ ጊዜ አወዳድሮ ማስገባት የሚሰጡ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ፖስታ በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1002 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ማቅረብ የሚችሉትን የምግብ ዓይነት ፍርድ ቤቱ ባቀረበው ሰነድ መሰረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡ በ15ኛው ቀን 10፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 19% የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ በፅሁፍ ከተገለፀ በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፊት ለፊት

 

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ/የሐዋርያው ጴጥሮስ ት/ቤት ለ2019ዓ.ም የበጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት...

READ MORE