የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸ/ዞን የመጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸ/ዞን የመጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ሎት 1፡- የጽ/መሳሪያ
- ሎት 2:- ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3፡- የኤሌክትሮኒክስ ቋሚና አላቂ እቃዎች
- ሎት 4:- ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5፡- ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች
- ሎት 6:- የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 7፡- የተሰፋ /የተዘጋጁ አልባሳት እና ጫማዎች ብትን
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከጥቅምት 10/07/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 25/2/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ብቻ ሲሆን ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችም፡፡
- ተጫራቾች የሞሉበትን ዋጋ በማስላት ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያስያዙትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድረገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የ/ሲፒኦ ከሆነ አርጅናሉ መቅረብ አለበት።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር በማያያዝ ኮፒና ኦርጅናሉን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉን የያዘውን ፖስታ ላይ ኦርጅናል ኮፒውን ፖስታ ላይ ኮፒ ተብሎ መፃፍ ይኖርበታል።
- በተጨማሪም የንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው።
- በሁለቱ ፖስታዎች ላይና እንዲሁም በጨረታ ዋጋ መሙያ የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ስም፡- ፈርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል እንዲሁም ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው ካለውም በፈሉድና ሌሎች ማጥፊያ ሳይጠቀሙ እንድ ስረዝ ብቻ በመጠቀም ፖራፍ በማድረግ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ በፍ/ቤታችን በመገኘት ከሎት 1- እስከ ሎት 7 ላሉት የውል ማስከበሪያ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝና ውል መፈፅም አለባቸው፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፅሙ በግዥ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን በመውረስ ለመንግስት ገቢ ያደረጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅና መመሪያው መሰረት አሸናፊነትና ተሸናፊነት በተገለጸ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት፡፡ ሁሉንም እቃዎች ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የኅዝብ በዓላት ፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዋ/ገ/ያዥ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጥል ፍ/ቤቱ በሚያዋጣው መልኩ ሲሆን በጥቅል ከሆነ በድምር ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈልጉ በስልክ ቁጥር፡- 0116850005/116850101 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት
