መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/ የግልጽ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ፡ ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የመኪና ዘይቶች፣ የመኪና ዲኮር ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣ የህንፃ ጥገና ዕቃዎች፣ የሴፍቲ ና አልባሳት እቃዎች፣ ማሽኖች፣ቱሎች እና መገልገያ እቃዎች
የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ
የግልጽ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ መለያ ቁጥር፡ መኢኢግ/ግጨ/01/2019
1. የግዥ ፈፃሚው ስም፡- መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/
2. የግዥው ዓይነት፡- ሎት አንድ፡- ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት ሁለት፡- የስቴሽነሪ ዕቃዎች
ሎት ሶስት፡- የፅዳት ዕቃዎች
ሎት አራት፡- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት አምስት፡- የመኪና ዘይቶች
ሎት ስድስት፡-የመኪና ዲኮር ዕቃዎች
ሎት ሰባት፡- የመኪና ጎማ እና ባትሪ
ሎት ስምንት፡- የህንፃ ጥገና ዕቃዎች
ሎት ዘጠኝ፡- የሴፍቲ ና አልባሳት እቃዎች
ሎት አስር፡- ማሽኖች፣ቱሎች እና መገልገያ እቃዎች
3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡
-የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Number) እና በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት ኦን ላይን የተመዘገበ ና የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
4, የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡-ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴል ማግኘት ይችላሉ::
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ሎት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው ይለቀቅለታል::
7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል::
8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበው ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል የድርጅታችሁ ማህተም የተመታበት፣ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው:: እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልጽ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል::
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም::
10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡30 የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በቀን አርብ ቀን 04 ህዳር 2019 ከጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን አርብ ቀን 04 ህዳር 2019 ከጠዋቱ 4:30 ይከፈታል::
11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ(--)ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም::
12. ግሩፑ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የእቃዎች ዝርዝር ፍላጎት ላይ ናሙና/Per Sample/ለተጠየቁት እቃዎች ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
13, ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0967 26 16 36
መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/
ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ቬራ ሆቴል አዲስ አባባ፣ ኢትዮጵያ
