የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለተለያዬ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ በዝርዝር የተቀመጡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የዕቃ ግዥ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለተለያዬ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት -
|
ተ.ቁ |
የጨረታው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
መግለጫ |
ተ.ቁ |
የጨረታው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
መግለጫ |
|
1 |
የጽ/መሳሪያ |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
11 |
የከባድ መኪና መለዋወጫ |
50,000 |
” |
|
2 |
የህንፃ መሳሪያ |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
12 |
የቀላል መኪና መለዋወጫ |
50,000 |
” |
|
3 |
የጽዳት ዕቃዎች |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
13 |
የማሽነሪዎች መለዋወጫ |
50,000 |
” |
|
4 |
ህትመት ሥራ |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
14 |
ሻይ ቡና መስተንግዶ ግዥ አቅርቦት |
70,000 |
TOT |
|
5 |
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
15 |
የጉልበት ሥራ ሎት1 ሎት2 ሎት3 |
70,000 |
ደረጃ 9 Gc-Bc |
|
6 |
ፈርኒቸር |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
16 |
አቅርቦት ሴሌክት ጠጠር አሸዋና ድንጋይ |
50,000 |
በዘርፉ ፍቃድ ያለው |
|
7 |
የኤሌክትሪክ ሞተሮች |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
17 |
ሞተር ሳይክል መለዋወጫ |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ የሆነ |
|
8 |
የቬንዝን ሞተሮች |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
||||
|
9 |
የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦት |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
||||
|
10 |
የግንባታ አጣናዎች |
50,000 |
VAT ተመዝጋቢ |
|
ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
- በዘርፍ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN No) ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት፣ ፍቃድ ያለው ያላት VAT ተመዝጋቢ የሆነ
- የአቅራቢነት ማስረጃ ኦን ላይን ማቅረብ የሚችል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ም/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ እንድትገዙ እንገልፃለን ፡፡
- ዋጋቸውን በማያሻማ መልኩ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን ፡፡
- የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሲሆን የሚከፈተው 4፡30 በከተማው በፋ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዕረፍት ከሆነ በቀጣይ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾቹ ጨረታ ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ 1/ እና ኮፒ 2/ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ፋይናንሻል ኮፒ 1 እና ኮፒ 2/ እንዲሁም CPO በፖስታ አድርገው በእናት ፖስታ አሽገው እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡
- ውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፤
- አሸናፈው ዕቃውን የሚያስረከብበት ቦታ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ሲሆን ማስጫኛና ማውረጃ የትራንስፖርት ወጪዎች በአሸናፊው ይሸፈናል።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ናሙና የማቅረብና የማስያዝ ግዴታ አለበት፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የዕቃው መጠን በሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት በ20% ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
