የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀከቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተሽከርካሪዎች የወንበር ልብስ፣መረጋገጫ፣ኩሽን እና የወለል ምንጣፍ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-PPM/06/2018(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀከቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተሽከርካሪዎች የወንበር ልብስ፣መረጋገጫ፣ኩሽን እና የወለል ምንጣፍ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ ፡፡
-
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. አ.አ.ኤ.አ.ፕ ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ _ በማድረግ _ ጨረታ ቁጥር EEU- PPM/06/2018 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ 8፡30 ላይ ይከፈታል::
-
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00 – 6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ ፡፡
-
የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
-
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111263159 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
