Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ-ከርስቲያን መግቢያ (ቀራንዮ አደባባይ) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118357484
  • Website
  • Deadline22 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 11 ቀን ቆይቶ በ 11 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather

በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ በወረዳ 08 ከልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 001/2019 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መግዛት እና የጭነት እና ለመዝናኛ ከበብ አገልግሎት የጥገና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡


የመደመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ በወረዳ 08 ከልል የሚገኘው የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 001/2019 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መግዛት እና የጭነት እና ለመዝናኛ ከበብ አገልግሎት የጥገና ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሎት1.የደንብ ልብስ ሎት2.አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት3.ህትመት ሎት4.የሕክምና እቃዎች ሎት5.የፅዳት እቃዎች ሎት6.የተለያዩ መፅሕፍት ሎት7.የላብራቶሪ እቃዎች ሎት8.ቋሚ እቃዎች ሎት9.የስፖርት መገልገያ ሎት10.ልዩ ልዩ መገልገያዎች ሎት11.የጭነትና ለጉልበት ሎት12.የመዝናኛ ከበብ አገልግሎት ሎት13.ማሸነሪ ጥገና እና ሰርቪስ ሎት14.የተገጣጣሚ እድሳት እና የህንፃ ጥገና ስራዎች

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
  2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. ተጫራቾች ይህን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት በየሎቱ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ የድርጅታቸውን ማህተም ያረፈበት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸገበት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በነጋት የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳይታሽጎ በዚያው አለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  6. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ በጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልጽና በዝርዝር በተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ከአስተባባሪ የተፈረመ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን ሎት1፡-35,000 ሎት2፡-3,000 ሎት3፡-5,000 ሎት4፡-1,200 ሎት5፡-20,000 ሎት6፡-6,000 ሎት7፡-12,500 ሎት8፡-60,000 ሎት9፡-42,500 ሎት10፡-6,000 ሎት11፡-9,000 ሎት12፡-30,000 ብር ሎት13፡-3,000 ሎት14፡-14,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  8. በጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ሲፒኦ በመውሰድ እና ተጫራቾች ውል እንዲዋዋሉ ከመ/ቤቱ ሲገለጽላቸው ያሸነፉበትን የዋጋ ድምር 10% በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  10. ጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ በጥራት የሚበልጥና ከመው ዋጋ ያለው ዕቃ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው በጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫ 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
  12. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡባቸው የተመረጡትን ዕቃዎች ናሙና እስከ ግልጽ ጨረታ ማለቂያ በነጋት የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. ተጫራቾች ከት/ቤቱ የወሰዳችሁትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በናንተ የሚሞሉ ክፍሎችን በመሙላት ተመላሽ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  14. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  15. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኙ ጨረታውን ከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከበዳአሎ በሆላንድ ኤንባሲ ወደ ወ/ዓለም ቀጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቀራንዮ አደባባይ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል ፍላንስ ጋር

ስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-69-84

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for uniforms, consumable office supplies, printing, medical items, cleaning materials, books, laboratory equipment, fixed assets, sports and miscellaneous supplies, plus transport, labour, recreational, maintenance and building repair services. Eligible bidders need a renewed trade licence, registration certificate and VAT registration.
Save Tender